ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ፕሬዝዳንት ሳልቫና ሬክ ማቻርን አወያዩ

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)- የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርና የተቃዋሚ መሪ ሬክ ማቻር የአገራቸው ሠላም የመጨረሻ ዕልባት እንዲያገኝ ያላቸውን ልዩነት እንዲየጠቡ አሳስቧቸዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ትላንት ምሽት በፅ/ቤታቸው ሁለቱን መሪዎች በነጋገሩበት ወቅት በዘመናት ትግል ነፃ የወጡትን ህዝብ ከሞት ፣እንግልት እና ስደት መታደግ አለባቸው ብለዋል።

ሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አዲስ አበባ ውስጥ ሲገናኙ ከሁለት ዓመት በኋላ ይህ የመጀመሪያ ነው።

የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በደቡብ ሱዳን ሠላም ላይ የሚመክር ስብሰባን ዛሬ ይመራሉ።

%d bloggers like this: